ማስታወቂያ

የሂሣብ ምርመራ አገልግሎት ኮርፖሬሽን በቅርብ ጊዜ ውስጥ በተለያዩ የክልል ከተሞች በተሰሩ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ለሚያከናውነው የክዋኔ ኦዲት በአማካሪነት የሚያገለግሉትን መሐንዲሶች አወዳድሮ በኮንትራት ቀጥሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ኦዲቱም በአብዛኛው በመስክ የሚካሄድ ይሆናል፡፡

ብዛት፡-                         8 (ስምንት)

ተፈላጊ ችሎታ፡-                 የመጀመሪያ ዲግሪ በሲቪል እንጂነሪንግ ወይም በኢንፍራስትራክቸር ኢንጂነሪንግ ያለው/ያላት ቢያንስ 10 ዓመት የሥራ ልምድ ሆኖ ከዚህ ውስጥ ቢያንስ 5 ዓመት በመሠረተ ልማት ግንባታና ፕሮጀክቶች በተለይም በከተሞች የውስጥ ለውስጥ መንገዶችና ኮብልስቶን ግንባታዎች የሰራ/የሰራች፡፡ የክዋኔ (Value for money) ኦዲት ልምድ ወይም መጠነኛ ዕውቀት ላለው/ላላት ቅድሚያ ይሰጣል፡፡

የኮንትራት ጊዜ፡-                 ለሦስት ወር (3 ወር)

ለመወዳደር የምትፈልጉ አመልካቾች የትምህርትና የሥራ ልምድ ማስረጃችሁን እንዲሁም ለአገልግሎቱ የምታስከፍሉትን ዋጋ የያዘና በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ካዛንቺስ ከዘመን ባንክ ጎን በሚገኘው ኮርፖሬሽናችን ቢሮ ቁጥር 203 እንድታስገቡ እያሳወቅን፣ ማስረጃዎቹ የሚቀርቡበት የጊዜ ገደብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ብቻ  ሆኖ ቅዳሜና እሁድን ሳይጨምር መሆኑን እንገልፃለን፡፡

አድራሻ፡- የሂሣብ ምርመራ አገልግሎት ኮርፖሬሽን (Audit Services Corporation)

        የስልክ ቁጥር 011 553 97 23/ 011 553 50 15/ 011 553 79 27

        የፖስታ ሳ.ቁ. 5720 አዲስ አበባ

        ካዛንቺስ ከዘመን ባንክ አጠገብ ያለው ህንፃ